top of page
Image by Greg Rosenke

 

ሥርዓተ ቅዳሴ / የቅዳሴ ሥርዓት

        ቤተክርስቲያናችን ሥጋወደሙን የምታከብርበት የተለየ ሥርዓተ ጸሎት አላት፡፡ ይህ ልዩ የምስጋና ጸሎት ሥርዓተ ቅዳሴ /የቅዳሴ ሥርዓት/ ይባላል፡፡ ያለ ጸሎተ ቅዳሴ ሥጋወደሙ አይዘጋጀም (አይፈተትም) ፤ ያለ ሥጋወደሙም ቅዳሴ አይቀደስም፡፡ ሥርዓተ ቅዳሴ የሚለውን ቃል ስንመለከት “ሥርዓት” ማለት አሠራር፣ አፈፃጸም ተብሎ የሚተረጎም ሲሆን “ቅዳሴ” ደግሞ ምሥጋና ማለት ነው፤ ይኸውም ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ምሥጋና ማለታችን ነው።

         

         የቅዳሴ ሥርዓት ካህናትና ምእመናን በአንድነት በመሆን ለአምላካችን ምስጋና የምናቀርብበት፣ ለበደላችን ይቅርታና ምሕረት የምንጠይቅበት፣ ኅብስቱና ወይኑ የሚለወጥበት የጋራ የጸሎት ክፍለ ጊዜ ነው ፡፡ በቅዳሴ ጸሎት “እግዚኦ ተሣሃለነ” አቤቱ ይቅር በለን ፤ “ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ…” አቤቱ በመንግሥትህ አስበን ፤ “ንዜኑ ሞተከ እግዚኦ ወትንሣኤከ ቅድስተ…” አቤቱ ሞትህንና ልዩ የሚሆን ትንሣኤህን እንናገራለን በማለት “እኔ” ብለን ሳይሆን “እኛ” እያልን ከፈጣሪያችን ጋር የምንገናኝበት የጸሎት ሰዓት በመሆኑ በቅዳሴ ጊዜ የግል ጸሎት የተከለከለ ነው።

 

           በቅዳሴ ጸሎት በመሳተፋችን የኃጢአት ስርየት እናገኛለን፤ በረከተ ሥጋም በረከተ ነፍስም እንታደላለን፤ ከሁሉም በላይ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን በልተን ክቡር ደሙን ጠጥተን የዘለዓለም ሕይወትን እናገኛለን።

በቤተክርስቲያናችን የታወቁና እስከአሁንም በአገልግሎት ላይ ያሉ ቅዳሴያት በዓይነት 14 ሲሆኑ ቀደም ባሉት ዘመናት በተለይ በወርኀ ጽጌ ይቀደስ የነበረ ‹‹መዓዛ ቅዳሴ›› የሚባል 15ኛ ቅዳሴም በቤተ ክርስቲያናችን ይገኛል፡፡

   

        14ቱ የቅዳሴ አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፣

1. ቅዳሴ ዘሐዋርያት / Kidasse the Hawariat

2. ቅዳሴ ዘእግዚእ / Kidasse the Egzi

3. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ

4. ቅዳሴ ዘእግዝእትነ ማርያም / Kidasse the Anaphora of Our Lady

5. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምእት

6. ቅዳሴ ዘቅዱስ አትናቴዎስ / Kidasse the Anaphora of St Athnasious

7. ቅዳሴ ባስልዮስ

8. ቅዳሴ ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ኤጲስቆጳስ ዘኑሲስ (የሆሣዕና ቅዳሴ)

9. ቅዳሴ ዘቅዱስ ኤጲፋንዮስ / Kidasse the Anaphora of St Epiphaneous

10. ቅዳሴ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ / Kidasse the Anaphora of St John Chrysostom

11. ቅዳሴ ዘቅዱስ ቄርሎስ

12. ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ

13. ቅዳሴ ዘቅዱስ ዲዮስቆሮስ / Kidasse the Dioscoros

14. ቅዳሴ ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ

bottom of page